የውስጠኛውን መንግሥት መጠበቅ
ጥቅስ፡ (ሉቃስ 11፡33-36)
እኛ የዓለም ብርሃን ደግሞም የምድር ጨው ነን። በክርስቶስ ብቻ የተገኘ ሰማያዊ ማንነት አለን።
በተራራ ላይ/ በከፍታ ልንቀመጥ፣ ብርሀናችንን ልንጠብቅ እና ልናበራ ተጠርተናል።
እግዚአብሔር እንድታይ፣ በየደረጃው ጨለማን ልትገፋ ፈጥሮሃል። ጠላት – ከሆነ ነገር በታች ሊደብቅህ ይፈልጋል፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ተገልጥ! ይለናል።
ስለ ውስጠኛው የሚደረግ ጦርነት፡
አስፈላጊ የሆነ ማስጠንቀቂያ – በውስጥህ ያለውን ብርሃን ጠብቅ!
የጠላት ስልት የልብህን መብራት — ለማጥፈት የተሰላ ዘመቻ ላይ ነው።
ኢየሱስ የዚህን ጦርነት ኮር ይገልጻል፡ “የሰውነትህ መብራት ዓይንህ ነው።” ይህ የልብህ ዓይን ነው (ኤፌ. 1፡18) — አመለካከትህ፣ ትኩረትህ እና ጥልቀት ያለው ግንዛቤህ። ይህ የውስጠኛህ ሰው ዙፋን ቤት ነው (ኤፌ. 3፡16)።
መንግሥተ እግዚአብሔር /entos/ በውስጣችሁ ነው (ሉቃስ 17፡21)። ያንን ውስጣዊ ቦታ የሚይዘው ይገዛሃል። ስለዚህ የውስጣዊ ማንነታችንን የሚያበላሹ እና ብርሃናችንን የሚያደበዝዙ ነገሮችን በጥንቃቄ መከላከል አለብን፡
- የአመለካከት መበላሸት – የዓለም በጣም ጠንካራ ጨለማ “ብዙ ገንዘብ፣ ብዙ ሕይወት” በማለት ማታለል ነው። በገንዘብ ብዛት እርካታና ደህንነት/security በማጠራቀም እንደሚገኙ የሚያምን አስተሳሰብ አለ። ይህ አመለካከታችንን ውስጣችንን ያበላሻል። ውስጣዊ ስምምነትህን ለማን ሸጠሀል? ጎበዙ ወጣት ገንዘብ ለተሻለ ሕይወት መንገድ እንደሆነ አመነ፣ ያ ማታለልም በሐዘን ተወው (ሉቃስ 18፡23)። ያንተ የተሻለ መንገድ ምንድን ነው? የውስጥ ዙፋንህ በመንግሥተ እግዚአብሔር ብቻ መያዝ አለበት፣ ገንዘብ መሣሪያ ነው፣ የምንኖረው ለዕለታዊ የኑሮ ፍጆታ አይደለም። አዎ ይህ አታጋይ እውነት ነው ግን እድገታችን ወደዚሁ ነው።
- ራስን የመውደድ መርዝ፡ ይህ የጨለማው ኃያል ሰራተኛ ነው። ሀብታሙ ሰው (ሉቃስ 12) በርካታ ምርቱን አይቶ ስለ ራሱ ብቻ አሰበ ትላልቅ መጋዘኖችን ገነባ። በልቡም ራሱን አብዝቶ ሊወድ ለራሱ ብቻ ሊኖር ተማማለ። በልባችን አስበን የምንኖርበት እምነታችን ምን ይሆን። ባለጠጋው የበረከቱን ምንጭና ዓላማ ረሳ።
ራሳችንን ከመንግሥቱ በላይ ስናገዝፍ፣ የተሰጠንን ልናበዛና ልናካፍል ከማሰብ ይልቅ እንደ ካህኑ ኤሊ ልንደልብ ስንጀምር፣ ዓላማችንን እናጣለን። በጨለማ ወጥመድ እንያዛለን።
የጠነከረ ራስን የመውደድ ኑሮን መገንባትና ለዛም ሁሉን በዙሪያው መደርደር እንጀምራለን። ይህም የውስጣችንን ዓይን ያሳምማል – እየቆየም ያሳውራል።
እናም በአኗኗራችን ጨለማው እየበረታ ጠላት የሚሰርቅበት፣ የሚገድልበትና የሚያጠፋበትን ሁኔታ ይፈጠራል።
- የተሳሳቱ ምኞቶች/መፈለግ።
ጠላት የውስጣዊ ማንነትህን ለመቆጣጠር ጦርነት በማድረግ የብርሃን መንግሥት እንዳይገለጥ ያደርጋል። ኢየሱስ በትምህርቱ ምኞታችንን እንደገና ለማስተካከል እንዲህ ይለናል :- ሕይወት ከምግብ ይበልጣል፣ ሰውነትም ከልብስ። (ማቴ. 6፡25)። ትልቁ ልንፈልገው የሚገባው እውነት መንግሥተ እግዚአብሔር ነው። ከሁሉ አስቀድመን በመጀመሪያ መንግሥቱን እንድንፈልግ ያዛናል።
በምድር ላይ ካሉት ጊዜያዊ ችግሮች በላይ ዘላለማዊውን መንግሥት ልንፈልገው ግድ ነው። ይህም ውስጣችንን ማለትም ዖይናችንን በብርሀን እንዲሆን ያስችለዋል። ሕይወትህ ዙሪያ የሚዞረው ምንድንነው? ትኩረትህ በታላቁ፣ የዘላለም እውነታ ላይ ነው ? ወይስ በጊዜያዊነት ሸክሞች ተይዟል? የተሳሳተ ትኩረት ወደ ጨለማ ይወስዳል። ትኩረትህ ዘላለማዊው መንግሥት ይሁን።
ምኞቶችህን እንደገና አስተካክል። ታላቁን ፈልግ። ሕይወትህን፣ ጭንቀቶችህን እና ጥረቶችህን በማያልቅ በመንግሥተ እግዚአብሔር ዙሪያ አድርግ።
ኢየሱስ ከፈሪሳውያን “እርሾ” እንድንጠንቀቅ ያሳስበናል። በውጫችን ስንታይ መንፋሳዊ መምሰልና በውስጣችን ግን ለገንዘብና ለሥጋዊነት መኖር ግብዝነት ነው። (ሉቃስ 12፡1)። ሃይማኖታዊነት ዋናው መልኩ ማስመሰል ድራማተኛ መሆን ነው።
መብራቱ የበራ ሰው የምንሆነው – በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከሰማያዊ አባታችን ጋር ያለን በመንፈስ ቅዱስ የሆነው ጥልቅ ውስጣዊ መያያዝ እና በውስጣችን ከሚገዛው ከመንግሥቱ ጋር በሚስማማ አኗኗር እየኖሩ በምድር ክብሩን በማብራት ስንኖር ነው።
ልታበራ ተዘጋጅተሃል። አሁን በውስጥህ ያለውን ብርሃን ጠብቅ። በጨለማ ውስጥ ላሉት ዓይን እንድንከፍት ተጠርተናል።
“ከጨለማ ወደ ብርሃን” እንዲሸጋገሩ።
(ሐ. ሥ. 26፡18)
አሜን። GK group (THEODOR BEY )
